Postlar filtri


ጠበቆች ሙያዊ የሚጠይቀውን ስነ ምግባር ጠብቀው በመስራት የፍትህ ስርዓቱን የማገዝና የህዝብን ጥቅም የማስከበር ኃላፊነት አለባቸው፡-

የምዕራብጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ እሱባለው መኮንን

መምሪያው ከምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ከፍኖተ ሰላም ከተማና አካባቢው ከሚገኙ ጠበቆች ጋር በፍትህ አስተዳደሩ ጠበቆች ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ያለመ የምክክር መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ እየተካሄደ ነው።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ እሱባለው መኮንን ጠበቆች የፍትህ ስርዓቱን በማሳለጥ ህዝብ የሚያምነው የፍትህ አስተዳደር እንዲገነባ በማስቻል በኩል የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

የጥብቅ ሙያ ትልቅ ክብር የሚሰጠውና ጥብቅ የሙያ ስነ ምግባር ጠብቆ የሚሰራ ነው ያሉት አቶ እሱባለው ጠበቆች ለሙያቸውና ህሌናቸው ተገዥ በመሆን የህዝብን ጥቅም የማክበርና የማስከበር ኃላፊንታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የጥብቅና ስራ ግለሰቦች በእውቀት ማነስ ምክንያት መብትና ጥቅሞቻቸው እንዳይጣስና አለመግባባቶችን በህግ የመፍታት ባህል እንዲጎለብት የማይተካ ሚና የሚወጡ በመሆኑ ጠበቆች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባልም ነው ያሉት።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አባይነህ ካሴ በበኩላቸው የፍትህና ዳኝነት ስርዓቱ በቅብብሎሽ የሚሰራ በመሆኑ ጠበቆች ሙያቸውን አክብረው በመስራት የህዝቡን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ ክርክሮች በአብዛኛው በጠበቆች አልፈው የሚመጡ በመሆናቸው ጠበቆች የጥብቅና ስነ ምግባርን ጠብቆው ባለ ጉዳዮችን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸውም ነው የገለጹት። Source:- West Gojjam Communication


በ2017 በጀት ዓመት ዳሪስ ሲስተምን (DARIS) ተፈጻሚ በማድረግ የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ስራዎችን በመተገበር የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የዕውቅና ሰርቲፊኬት  አገኘ


ይህ መፅሐፍ በቀጣይ ሳምንት በገበያ ላይ ይውላል ገዝተው ያንብቡ - ግብዣችን ነው።


የሕግ ባለሙያዎች ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ እንዲሠሩ ተጠየቀ።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም የሕግ ባለሙያዎች ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት በዓለም አቀፍ ወንጀሎች ምርመራ እና ክስ ሂደት አመራር ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለአማራ ክልል ዓቃብያነ ሕግ ሥልጠና እየሠጠ ይገኛል።

የዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ ማለት ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን ለመከልከል እና መንግሥታት ወንጀሎችን እንዲከሱ እና እንዲቀጡ ግዴታ ለመጣል የተነደፈ የዓለም አቀፍ ሕጎች አካል ነው።

የዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ወንጀል የተገለጹ ድርጊቶችን ይከለክላል፤ የሀገራትን ግንኙነት እና የግለሰቦችን ኀላፊነት ይመለከታል፤ የሕግ ጥሰት ከተከሰተ የወንጀል ተጠያቂነት ያስከትላል።

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኀላፊ አያሌው አባተ (ዶ.ር) እንዳሉት የዘር ማጥፋት፣ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል፣ የጦር ወንጀል እና የወረራ ወንጀል ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ተብለው የተለዩ ናቸው።

ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ከፈጻሚዎች ባሕርይ፣ ከሚያደርሰው ጉዳት፣ ከወንጀሉ የአፈጻጸም ረቂቅነት እና ከተጎጅዎች ባሕርይ ጋር ሲታይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ናቸው።

ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ካላቸው ውስብስብነት ባሕርይ አኳያ ሥልጠና መሥጠት ማስፈለጉንም ገልጸዋል።

ሥልጠናው በዓለም አቀፍ ወንጀሎች ምንነት፣ በምርመራ ሂደት እና ሥልት፣ ምርመራው እንዴት ሊመራ እንደሚገባ፣ ክሱ በሚዘጋጅበት ወቅት ሊያሟላቸው የሚገቡ መሠረታዊ ነገሮች፣ በክሱ ሂደት ላይ ሊታዩ የሚገባቸው ዓለም አቀፍ የሕግ ድንጋጌዎች እና የሀገር ውስጥ ሕጎች ምንነት ላይ ያተኮረ ነው።

በቀጣይ ወንጀሎች ተፈጽመው ከተገኙ ዓለም አቀፍ የሕግ መርሆችን በመከተል ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሥራ የሚሠራ ይኾናል ብለዋል።


የሥልጠናው ተሳታፊ ወንድወሰን ይፍሩ እንዳሉት በዓለም አቀፍ ወንጀል እና ሕጉ ምንነት ላይ የሚሰጡ ሥልጠናዎች የባለሙያዎችን የምርመራ አቅም የሚያሳድጉ ናቸው። በተለይም ደግሞ አሁን ላይ በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ካሉ ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ የሚያግዝ መኾኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው ሠልጣኝ ደረጀ ቁምላቸው እንዳሉት ደግሞ ከሀገር አቀፍ ሕጎች ባለፈ በዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የባለሙያዎችን ሁለንተናዊ የሕግ እውቀት የሚያሳድጉ ናቸው።

ከአካባቢያዊ ባለፈ ዓለም አቀፋዊ ወንጀሎችንም በመመርመር ለሕግ የበላይነት መከበር እና ለፍትሕ መስፈን አቅም ይፈጥራሉ ብለዋል።

አሚኮ






የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ም/ዋና ዕንባ ጠባቂ ክቡር የኔነህ ስመኝ (ዶ/ር) የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ጎበኙ። የአብክመ የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ደሴ ጥላሁን (ዶ/ር) እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ክቡር ም/ዋና እንባ ጠባቂው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን የስራ እንቅስቃሴ አስመልክት ከሰራተኞች ጋር ውይይት በማድረግ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአርማ ለውጥ አደረገ



አርማው ያካተታቸው ምልክቶች ትርጓሜ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. በአርማው ላይ የሚታዩት ሰዎች

ቆመው የሚታዩት ቆፍጣና እና ንቁ ሴት እና ወንድ በአንድ እጃቸው ጋሻ አንግበው፣ በሌላ እጃቸው ደግሞ የፍትሕ ምልክት የሆነውን ሚዛን የቆመበትን ምሰሶ ይዘው ይታያሉ፡፡ ይህም የክልሉ ህዝብ ለሕግ ተገዥ በመሆን የሕግ የበላይነትን ለማክበርና ለማስከበር በጽናት እና በቁርጠኝነት ዘብ መቆሙን ያሳያሉ፡፡ ፍትሃዊነትንና እኩልነትን እውን ለማድረግ የማይዋልል ጽኑ አቋም ያለው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያስረዳል፡፡ በሌላው እጃቸው አንግበው የያዙት ጋሻ ደግሞ የፍርድ ቤቶችን ነጻነት በማስከበር ነጻ፣ ገለልተኛ እና ብቃት ያለው የዳኝነት ሰጪ አካል በመገንባት ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ የመብት ማስከበሪያ ተቋማት መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ ከህዝቡ አብራክ የተገኙ በየደረጃው በሚገኙ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚሰሩ ዳኞች በሰዎች መካከል አንዳች አይነት ልዩነት ሳያደርጉ ሕግንና ማስረጃን ብቻ መሰረት በማድረግ የሕግ የበላይነትን እና ፍትሕን ለማስፈን ያላቸውን ቁርጠኝነትና ጽናት ያሳያሉ፡፡ ዳኞች እውነትን ለማፈላለግ ሀቀኛ፣ ትጉህና ታታሪ፣ ብልህ፣ ደፋር እና ቁርጠኛ መሆን ያለባቸው መሆኑንም ያስረዳል፡፡

2. የዳኛ ወንበር

በሁለቱም አቅጣጫ ከጋሻው እስከ ደረጃዎቹ ያሉት ምልክቶች የዳኞችን ወንበር ያመለክታሉ፡፡ ይህም ዳኞች ህዝብን በሀቀኝነት፣ በትጋትና ታታሪነት ለማገልገል ከህዝብና ከመንግስት የተጣለባቸው ከባድ ኃላፊነት መኖሩን ያሳያል፡፡ ፍርድ ቤቶች የፍትሕ ምልክቶች እና አደባባይ መሆናቸውንም ይጠቁማል፡፡ ዳኝነት ሰፊ የመወሰን ፍቅድ ስልጣን (wide Discretionary Power) የሚያጎናጽፍ መሆኑንም ያመለክታል፡፡

3. ከጋሻው ጋር የተሰፋው ክብ ምልክት

ክብ ምልክቱ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የህዝብ መገልገያ ተቋማት መሆናቸውን፣ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ መሰረታቸው ሩህሩህነት፣ ተንከባካቢነትና ሰብዓዊ ክብር፣ ቅንነት፣ ታማኝነት፣ ሀቀኛነት፣ ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት እና መሰል የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫዎች መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ ሕግና ሥርዓትን በማስከበር ረገድ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን የማይተካ ሚና ያስረዳል፡፡ እንዲሁም በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ክብ ምልክት እርቅ ተኮር ፍትሕን (Restorative Justice) ጽንሰ ሀሳብ የሚወክል መሆኑን የተለያዩ ጽሁፎች ያስረዳሉ፡፡

4. ከስር ያለው ደረጃ

ደረጃው፣ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉን ፍርድ ቤቶች፣ ህዝቡ ለፍርድ ቤቶች ያለውን ከፍ ያለ ክብር፣ ከዳኞች የሚጠበቀውን ከፍ ያለ ኃላፊነት እና ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ የመብት ማስከበሪያ የፍትሕ አደባባይ እና አለኝታ መሆናቸውን በጉልህ ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ደረጃው የይግባኝ ሥርዓትን ይጠቁማል፡፡ ጭነት ቢያጋድል በመጫኛ፣ ፍርድ ቢያጋድል በዳኛ የሚል ድንቅ ብሂል ያለው የክልሉ ህዝብ እውነትን ለማፈላለግ እና ፍትሕን ለማስፈን እስከ መጨረሻው በጽናት የሚሟገት መሆኑን ያስረዳል፡፡

5. ሚዛን

ሰዎች ያሉበትን ቦታ እኩል ከፍሎ የሚያልፈው የፍትህ ሚዛን የክልሉን ፍርድ ቤቶች ሕግንና ማስረጃን ብቻ መሰረት በማድረግ፣ የእኩልነት መርህን በመከተል ያለ አንዳች ልዩነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆነው ፍትሕ የሚሰጡ መሆናቸውን ያሳያል፡፡

6. ካባ

ከባ የክብር፣ የአስተዋይነት፣ የብልህነት፣ የብስለት፣ የአስታራቂነት እና የሸምጋይነት ምልክት ነው፡፡ የክልሉ ህዝብ ለሚወደው እና ለሚያከብረው የሚያበረክተው ልዩ ስጦታ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ዳኞች ጉዳዮችን በብልሀት እና በአስተዋይነት መመርመር ያለባቸው መሆኑን ከማሳየቱም በላይ ዳኞች ባለጉዳዮችን ማክበርና ትህትና የስራቸው መመሪያ ማድረግ ያለባቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡

ጥለቱ እና ባህላዊ ይዘት ያላቸው ሌሎች ምልክቶች ደግሞ የክልሉ ህዝብ ዘመናትን ያስቆጠረ የዳበረ ባሕል ባለቤት መሆኑን እና ባሕላዊ የአለመግባባት መፍቻ መንገዶችን ጨምሮ ሌሎች አማራጭ የአለመግባባት መፍቻ ሥርዓቶችን ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች በተጓዳኝ መተግበር የሚያሻ መሆኑን ያሳያሉ፡፡






Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


የኢትዮጵያን የፍትህ አገልግሎት ወደ ዲጂታላይዝ ስርዓት የመቀየር ስራ እየተከናወነ ነው - አቶ ቴዎድሮስ ምህረት

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2017፦ የኢትዮጵያን የፍትህ አገልግሎት ወደ ዲጂታላይዝ ስርዓት መቀየር የሚያስችሉ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ገለጹ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን(ዶ/ር) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዲጂታል እና ኢንፎርሜሽን ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፍርድ ቤቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

22 የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በኔትወርክ የማስተሳሰር ተግባር፤ የምስል ድምፅና መቅረጫ እንዲሁም ንግግርን ወደ ፅሁፍ መቀየር የሚያስችሉ መሳሪያዎች የተሟሉለት የስማርት ኮርት አገልግሎት እና ታራሚዎች ባሉበት ሆነው ችሎት የሚከታተሉበት የኢ-ኮርት ሲስተም የመዘርጋት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁሉም ፍርድ ቤቶች በጋራ የሚጠቀሙበት በይነ መረብ የማበልፀግ፣ እንዲሁም ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የሚፈልጉትን መረጃ ስልካቸውን በመጠቀም ማግኘት የሚያስችላቸው መተግበሪያዎች ዝግጅትና ሌሎች ተያያዥ ተግባራት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የተጀመሩት የቴክኖሎጂ ሪፎርም ስራዎች ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያን የፍትህ አገልግሎት ወደ ኢ-ኮርት(E-Court) ስርዓት ማሸጋገር የሚያስችል መሆኑን ነው ፕሬዚዳንቱ ያመለከቱት።

የፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሀን(ዶ/ር) በፍትህ ዘርፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ልማትና አጠቃቀምን ለማሳደግ በሶስት አመት የትራንስፎርሜሽ እቅዱ በትኩረት እየተሰራ የሚገኝ ዘርፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

ተቋማት ዘመኑን የሚመጥን ስራን ማከናወን የሚያስችላቸውን አቅም ፈጥረው የእርስ በርስ ጥምረትን በመፍጠር ወቅቱ የሚፈልገውን አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል።

የፍትህ ተቋማትን በቴክኖሎጂ አስተሳስሮ አገልግሎቱን በመስጠት የተጠያቂነት ስርዓት ለማስፈን እንዲሁም በደንበኞች ላይ የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን ማስወገድ የሚቻልበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።


Ethiopian_News_Agency



13 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »